ከዚህ ቀደም ላዳረጋችሁት አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡ ላደረጋችሁት ትብብር ምሰጋናችንን ለመግለፅ የለጋሾች ስም ዝርዝር በአዲስ በተሠራው ህንፃ በግድግዳ ላይ ስማችሁ እንዲቀረፅና ማስታወሻነቱ ለረዥም ጊዜ እንዲሆነ አሰተባባሪው ቡድንና በጎንደር የትምህርት ቤቱ አሠሪ ኮሚቴ የወሰኑ መሆናቸውን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
1. ሰማችሁ እንዳይቀረፅ የምትፈልጉ ከሆነ
2. ስማችሁ እናንተ በመረጣችሁት መንገድ እንዲፃፍ የምትፈልጉ ከሆነ
3. የሥራ ወይም የሙያ ማዕረግ እንዲጨመር የምትፈልጉ ከሆነ
4. ስም የለሽ (Anonoymus) ብላችሁ የለገሳችሁ ግን ስማችሁ እንዲፃፍ የምትፈልጉ ከሆነ
5. የስም ዝርዝር ውስጥ ስማችሁን ፈልጋችሁ ድንገት ያልተካተተ ከሆነ
በዚህ ኤሜይል አድራሻ መልክታችሁን በመላክ እንድታስታውቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡
አስተባባሪው ቡድን
ለማንኛውም የህንፃው ግንባታ እየተጠናቀቀ ቢሆንም ትምህርት ለመጀመርና ለማካሄድ በቂ ዝግጅትም ሰለሚያስፈልግ
በጊዜው በተለያዩ ምክንያት የመለገሥ ዕድሉ ካላጋጠማችሁ፣ በጎፈንድሚ GoFundme በኩል አስተዋፅኦ ማድረግ እንደምትችሉ በትህትና እናሳስባለን፡፡
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.