•የመጀመሪያው ዘመናዊ ት/ቤት የተገነባው በ1934 አ.ም.
•በዚያን ጊዜ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ጠቅላላ ቁጥር 100 ነበር
•በ1949 -1956 ከ9-12፣ የተማሪዎች ቁጥር 450 ነበር
•በአንድ ክፍል ውስጥ የነበረው የተማሪዎች ቁጥር፣ ለ9-10ኛ ክፍል 30 ሲሆን፣ ለ11-12ኛ ክፍለ 22 ነበር
•ከ1960 ጀምሮ ከአሜሪካ መንግሥት ርዳታና ትብብር ያገኝ ነበር፡፡ በ1963 የአሜሪካ ፒስ ኮር ያሰተምሩበት ነበር
•ዘመናዊ የአሜሪካን ቤተ መፃህፍትም ነበረው
•በ1966 በደርግ ዘመን ት/ቤተ ወደ ፋሲለደስ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ተቀየረ
•በተከተለው በኢህአደግ መንግሥት፣ በአዲሰ ፖሊሲ ወደ መሰናዶ ት/ቤት ተቀየረ
•አሁን የት/ቤቱ ተማሪዎች ቁጥር 2784 (ወንዶች 1325፣ ሴቶች 1459)
•እንደ 2010 ህዝብ ቆጠራ የጎንደር ከተማ ህዝብ ቁጥር 371350 (192 903 ሴቶች፣ ወንዶች 178 447)
የወቅቱ የትምህርት ቤቱ አቅም
39 መማሪያ ክፍሎች
1 ቤተ መፅሐፍ
1 ወርክሾፕ
2 መፀዳጃ ቤቶች
3 ኮምፒውተር ማዕከሎች
2የትምህርት አዳራሾች
ችግሮቹ?
•በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ በአንድ ክፍል የተማሪዎች ቁጥር 40 ነው
•የፋሲለደስ ት/ቤት ግን በአንድ ክፍል ከ70-106 ተማሪዎች ይቀመጡበታል
•ይህ በራሱ ትምህርት አሠጣጥ ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል
•የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያውን ከተከተለ፣ ት/ቤቱ 70 የመማሪያ ክፍሎች የግድ ያስፈልጉታል
•አሳዛኝ ሆኖ አብዛኞቹ መማሪያ ክፍሎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል
•አግልግሎት ላይ ያሉት በአስጊ ደረጃ ይገኛሉ
ምን ይደረግ?
•ነገሩን የሚያከፋው፣ በ2020 የተማሪዎችን ቁጥር ለማሰተናገድ የመማሪያ ክፍሎች ብዛት ወደ 94 ማደግ ይኖርበታል (አሁን ከደከመው ህንፃ ጋር 39 ክፍሎች)
•በህብረተሰብ ውስጥ ማስተካከያው ወይም ማበላለጫው ትምህርት ከሆነ
•በዚህ ሂደት ብዛት ያለው ተጎጂ ትውልድ ወደ ኋላ ይቀራል
•ስለዚህ የዚህ ችግር መፍትሄ መጭዎችን አመታት ግምት ውስጥ በማስገባት ዘለቄታ ያለው መሆን አለበት
አዲስ ት/ቤት መገንባት አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው
የተጀመረው እንዳይቋረጥ አብረን እንጨርስ
የተቻለዎትን በመለገሥ የተጀመረውን ግንባታ እናስጨርስ
ለአሁኑ ትውልድና ለመጨው ትውልድ የበኩልዎን ይተባበሩ
የተማሩበት ከሆነ ድርሻዎን ይወጡ ለሌሎች ተመራቂዎች መልክቱን ያጋሩ
በሌላ መንገድ መርዳት ከፈለጉ
መነን ተስፋሁንን ያነጋግሩ 408 228 2243
Copyright © 2024 Fasiledes School Project - All Rights Reserved.
Powered by GoDaddy
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.