• Home
  • Donors ለጋሾች
  • letter
  • Funding
  • School History
  • Comments
  • Calls
  • More
    • Home
    • Donors ለጋሾች
    • letter
    • Funding
    • School History
    • Comments
    • Calls
  • Home
  • Donors ለጋሾች
  • letter
  • Funding
  • School History
  • Comments
  • Calls

Inaugration ምረቃ letter

  

ለተወደዳችሁ ለዚህ ምረቃ በአል ተሳታፊዎችና በስፋትም ለአዲሱ የትምህርት ቤት ህንጻ ግንባታ በተለያየ መልክ አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ በሙሉ


በመጀመሪያ ለዚህ ደረጃ በመድረሳችን የተሰማንን ደሰታና ርካታ እያካፈልን በዚህ የግንባታ ሂደት እንድንሳተፍ ዕድሉን በማግኘታችን ደስታችን ድርብ ርካታችን ዕጥፍ እንዳደረገው ለመግለፅ እንወዳለን፡፡


በውጭ የምንኖር የድሮ ተመራቂዎችና ሌሎችም ተቆርቋሪዎቸ ያገኘነውን ዕድል በመጠቀም የግንባታ አስተባበሪ ቡደን በማቋቋም በተለያየ መልክ የገንዘብ ርዳታ በማሰበሳብ የተቻለንን ጥረት ማድረጋችን ግልጽ ነው፡፡ በተለይም ለህንፃው መጀመር መነሻ የሆነውን ሀብት በትጋትና ያለምንም ማሰለስ ትምህርት ቤቱን ለማሠራት ከታተሩት አሠሪ ኮሜቴዎች ጋር በግልፅና ተጠያቂነት በተመላበት ሁኔታ ገንዘቡን በመላክ ፐሮጀክቱ አንዲጀመር አድርገናል፡፡ 

የዚህ ፕሮጀክት አጀማማር መነሾው እንደሚታወቀው በጎንደር የሚገኘው ኮሜቴና ሌሎች ባለጉዳዮች ሲሆኑ፤ በውጭ ኗሪዎች በኩል ደግሞ የፋሲለደስ መረደጃ ማህበር ነው፡፡ ሰፋ ባለ ሁኔታ ለመስራት በማቀድ የወቅቱ የጎንደር ከተማ ከንቲባና ሌሎቸ ልኡካን ቡድን በተገኙበት በሰሜን አሜሪካ የፋሲለደስ ግንባታ አሰታባባሪ ቡድን ተቋቁሞ ስራውን ጀመረ፡፡ የፋሲለደስ መረደጃ ማህበር በነበረው ከታክስ ነጻ የሆነ የበጎ አድራጎት ተቋምነቱ፣ በአሰተባባሪው ቡደን በኩል ለሚሰበሰበው ገንዘብ የተለየ አካውንት በመክፈትና ብሎም ለግንባታው የሚውለውን ገንዘብ በመላክና በመቆጣጠር ታላቅ አስተዋጽኦ በማደረግ፤ የመረዳጃ ማህበሩ አባለትም የአስተባባሪው ቡድን አባል በመሆን ያገለገሉ በመሆናቸው ለፋሰሲለደስ መረዳጃ ማህበር ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ 


የገንዘብ አሰባሰቡና አላላኩ ግልጽና ህጋዊ በሆነ መንገድ የተካሄድ ለእያንዳነዱ ወጭ ከጎንደር አሠሪ ኮሜቴ የሚላኩ መረጃዎችን በማመሳከር የተሰራ ሲሆን፣ በተጨማሪም ከገንዘብ አሰባሰቡ ጀምሮ እሰከተላከበት ቦታ ድረስ በአሜሪካ መንግሥት ኦዲት የሚደረግ ሄደት አንደሆነ ለማስታወቅ እንወዳለን፡፡ አሰተባባሪው ቡድን የሚላከውን ገንዘብ አፅዳቂና ገንዘብ ላኪው የተለያዬ ግለሰቦች እንዲሆኑ በማድረግ ሄደቱን ጥንቃቄ የተመላበት እንዲሆን አድርጓል፡፡ በዚህም የጎንደር አሠሪ ኮሚቴ ላደረገው ሀላፊነት የተሞላበት የገንዘብ አጠቃቅም ሂደት ምስክርነት አንሰጣለን፡፡


የገንዘብ ማሰበሰቢያ ዘዴዎችም በጨረታ፤ በየከተሞች በአሰተባባሪው ቡድን አበላት መሪነት የገንዘብ ርዳታ ስበሰባዎቸ በማድረግ፣ በአዳራሽና በዙም ስብሰባዎቸ፣ አንዳንድ ቁሳቆሶችንም በሸያጭ በማቅረብ የተካሄደ ሲሆን፣ ዋናው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ የሆነው ግን ጎፈንድሚ ተብሎ በሚጠራው ማሰባሰቢያ ነው፡፡

በዚህም የቀድሞ ተማሪዎቸና ቤተሰቦቻቸው፣ ተቆርቋሪ ግለሰቦች በተጨማሪም የጎንደር ህክምና ሳይንስ የቀድሞ ተመራቂዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ከልብ የመነጨ ምስጋና እያቀረብን እንኳን ደስ ያለን እንላለን፡፡


ይህ ፕሮጀክት እንደተመኘነውና እንዳሰብነው ሳይሆን በተለያየ ምክንያቶች እየተጓተተ አንደነበር ለሁላችንም ግልፅ ነው፡፡ በጎፈንድሚው አስተዋጽኦ ያደረጉት ሰዎች ቁጥራቸው ያነሰ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦች የአሰተባባሪው ቡድን አባላትን ጨምሮ በተደጋጋሚ የገንዘብ አስተዋፅኦ በማድረግ ከፍተኛ የተቆርቋሪነት ሰሜታቸውን አስመስከረዋል፡፡ ሆኖም ይህ ፕሮጀክት እንዲገባደድና ለዚህ እንዲበቃ ላደረጉት በሀገር ቤት የሚገኙ ግለሰቦችና ድርጅቶች፤ አስተባባሪ ቡድኑ አንደ ሌሎች ሁሉ ፕሮጀክቱ የኔ ነው ብሎ ሲለሚያምን፣ ላበረከቱት ታላቅና ወwሳኝ አስተዋጽኦ ከልብ የመነጨ ምሰጋና ያቀርባል፡፡ በዚህ ላይ ግን ይህ ትብብር አንዲፈጠርና ሥራውም እንዲጠናቀቅ በቅርብ ክትትል በማድረግ ቀደም ብለውም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ ሀላፊነታውን የተወጡትን የተከበሩ ሚኒስር አቶ መላኩ አለበልን በቃላት መግለጽ ሊበቃ በማይቻልበት ሁኔታ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ የህንጻው መጠናቀቅን ርግጠኛ አንድንሆንና ይልቁንስ በትምህርቱ ላይ እንድናተኩር ሃሳብ በመስጠታቸው ትኩረታቸን ወደሌላ የተቀደስ አላማ እንድንቀይር ረደቶናል፡፡


የአስተባባሪው ቡድን ከህንፃ ግንባታ ወደ ትውልድ ግንባታ የሚል መርህ በመከተል በ2017 ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሚቀርቡ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት አንዲሠጣቸው የነበረን መጠነኛ ገንዘብ በተጨማሪም ራሳችን የአሰተባባሪ ቡድን አባላት ተጨማሪ የገንዘብ አስተዋፅኦ በማድረግ፣ በገንዘብ አያያዝና አጠቃቀማቸው አስተማማኝ በሆኑት በጎንደር አሠሪ ኮሜቴ በኩል ወጭ በማድረግ በተሠጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ከ90 % በላይ ተማሪዎች ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ ያስቻላቸው በመሆኑ የተሰማንን ገደብ የሌለው የርካታ ስሜት ለሁላችሁም ስናካፍል ስሜቱ የጋራ መሆኑን እየተረዳን ነው፡፡ 

ይህ የማጠናከሪያ ትምህርትም ለ2018 ተፈታኞች እንዲሠጥ በማድረግ የገንዘብ አሰተዋፅኦ በማድረግ ላይ ነን፡፡ በዚህም ተመሳሳይ ወይም የተሻለ ውጤት እንደሚመዘገብ ተስፈኞች ነን፡፡ ለዚህ ውጤት መብቃት የትምህርት ቤቱ መምህራንና ርዕስ መምህሩን እንኳን ደስ ያለን በማለት ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡

ይሀ የደረስንበት ውጤት አስደሳችና የሚያኮራ ቢሆነም መነሻ እንጂ መድረሻ አይደለም፡፡ ለወደፊትም የወጣቶቸን ህይወት በሚቀይረው ትውልድ ግንባታ ላይ ለሚደረገው ትኩረት ሁላችንም የበኩላችን አስተዋፅኦ እንደምናደርግ ታላቅ ተስፋ አለን፡፡ 


የፋሲለደስ ት/ቤት ግንባታ አስተባባሪ ቡድን

ሰሜን አሚሪካ

ጥር 8፣ 2018 ዓ.ም

Copyright © 2026 Fasiledes School Project - All Rights Reserved.

Powered by

This website uses cookies.

We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.

Accept