The New Fasiledes High School Building
ከህንፃ ግንባታ ወደ ትውልድ ግንባታ

ከህንፃ ግንባታ ወደ ትውልድ ግንባታ


The new Fasiledes High school builidng soon to start.
Students who go additional tuition for the school leaving exam passed at an unbelievable rate. (75 - 90% pass)

Our group is made up of committed volunteer individuals.
Founding Core Executive Committee
Past Advisory members

የፋሲለደስ ግንባታ አስተባባሪ ቡድን፣ ከህንፃው ግንባታ በተጨማሪ፣ በትምህርቱም ላይ በማተኮር፣
ለህንፃ ማሠሪያው ከተሰበሰበው ጎፈንድሚ ከተረፈች ትንሽ ገንዘብና በተጨማሪም የአስተባባሪው ቡድን አባላት በየግላቸው ተጨማሪ አስተዋፅኦ በማድረግ፣ የፋሲለደስ ቁጥር 1ና 2 ተማሪዎች ለ2017 መልቀቂያ ፈተና እንዲዘጋጁ በጀት በመመደብ፣ በት/ቤቱ አሠሪ ኮሜቴ፣ በርዕሰ መመህሩና በመምህራኑ በኩል የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሠጣቸው ተደርጎ የተገኘው ውጤት ሁሉንም ዜጋ የሚያስደስት መሆኑን ለመጋራት እንወዳለን፡፡
በመረጃ በርዕሰ መምህሩ በእንዳለ ታደሰ ወልደስላሴ በተላከልን የተማሪዎችን ውጤት ለማሳወቅ በሚል ደብዳቤ
ውጤቱ እንደሚከተለው ነው
በፋሲለደስ ግንባታ ቁጥር 1 ትምህረት ቤት ለ300 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት የተሠጠ ሲሆን፣ ከነዚህ መሀከል 270 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዝገበዋል፡፡ በፐርስንት ሲታይ ዘጠና ፐርሰንት (90%)
በተጨማሪም ከነዚህ መሀከል 15 ተማሪዎች ከ 495 – 534 ከፍተኛ ነጥብ አግኝተዋል፡፡
ሁላችንም እንኳን ደስ ያለን
የፋሲለደስ ቁ 2 የተወሰኑ ተማሪዎችም የማጠናከሪያ ትምህርት የተሠጣቸው ሲሆን ዝርዝሩ ለጊዜው ባይደርሰንም
ባጠቃላይ በቁጥር 1ና2 500 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ተሠጥቷቸዋል፡፡ ከቁ 2 ጋር ሲደመር ለዩኒቨርሲቴ ያለፉት ተማሪዎች 377 ነው፡፡ ይህም በፐርሰንት ሲታይ 75.5% ነው፡፡
እንደገናም አንኳን ደስ ያለን፡፡
ፈተናውን ላለፉና ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡት በተለይም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት ወጣቶች መጠነኛ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ሰለተጠየቀ፣ ባክዎን የሚችሉትን ይለግሱ፡፡
ይህንን ተግባራዊ የሆነ መልካም ውጤት ለተመለከተ ዜጋ ለአመታት በትምህርት ወደኋላ ለተጎተቱት ወንድምና እህቶቻችን
ልጆቻችን በዚህ በኩል ርዳታ ማድረግ የተቀደሰ ተግባር መሆኑን እንደሚረዳ ግልጽ ነው፡፡
የዚህ አይነቱ በጎ፣ ውጤታማ የሆነ፣ የዜጎችን ህይወት የሚቀይር ርዳታ ቀጣይነት ሊኖረውም ይገባል፡፡
ሰለዚህ ቅን ፍላጉቱ ላላችሁ ሰዎች በጎፈንድሚ በኩል በሚደረገው አስተዋፅኦ ርዳታ እንድታደርጉ በትህትናና በአክብሮት አንጠይቃለን፡፡
እባክዎ ይህንን መልካም ዜና ያጋሩ
የፋሲለደስ ግንባታ አስተባባሪ ቡድን በአሜሪካ
ምንም እንኳን እያዘገመም ቢሆን የፋሲለደስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአዲስ ህንፃ ግንባታው ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን በቅን አሳቢና ተቆርቋሪዎች አማካኝነት በተደረገ ርብርብ፣ የህንፃው ግንባታ እየተገባደደ በቅርቡ ተጠናቆ ለአግልግሎት የሚደርስ መሆኑን ስንገልፅ በትልቅ እፎይታና ደስታ ነው፡፡
በአሜሪካ የሚገኘው የግንባታው አስተባባሪ ቡድን በተጨማሪ ያደረገው ቢኖር፣ ለዚህ አመት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ለፈተና እንዲዘጋጁ በማለት፣ ጎንደር በሚገኘው የህንፃው አሠሪ ኮሚቴ ጋር በመተባበር፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን ለተማሪዎቹ የፈተና መዘጋጃ ትምህርት እንዲሠጡ በማድረግ በጀት መድቦ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ አድርጓል፡፡ ለዚህም ሲባል 1.2 ሚሊዮን ብር አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ወጭው የተሸፈነው ከግንባታ አስተባበሪው ቡድን በተላከ ገንዘብ ነው፡፡
የህንፃው መጠናቀቅ ለሁላችንም ታላቅ ስኬት ቢሆንም፣ ትምህርት በጥራት እንዲሰጥ ለማድረግ፣ በተለይም ከዚሁ ት/ቤት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ ጥረት እንደሚያሰፈልግ ሁላችንም እንገነዘባለን፡፡ ሰለዚህ ሁሉም በበኩሉ ለዚህ አስፈላጊ ለሆነ ትምህረትን ለማዳበር በሚደረገው ጥረት ድርሻውን እንዲወጣ ስንጠይቅ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡ የገንዘብ አስተዋፅኦ ለማድረግ ለሚፈልጉ ለዚሁ ለት/ቤቱ ማሰሪያ በተከፈተው የጎፈንድሚ አካውንት ርደታ ማድረግ የሚችሉ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡
ከምስጋና ጋር
አሰተባባሪ ቡድን


Stake holders:-
የተለየ አዲስ ለመስራት ሳይሆን ለአመታት ብዙ ተማሪዎችን ያስመረቀው የፋሲለደስ ት/ቤት ህንፃ በማርጀቱ የትምህርት ገበታ ላይ ባሉ ተማሪዎችና መምህራን እላያቸው ላይ ይናዳል የሚል ሥጋት በመፈጠሩ፣ በተጨማሪም በዚህ ሥጋት ምክንያት አንዳንዶች ህንጻዎች ለአገልገሎት እንዳይውሉ መታገዳቸውን በመመልከት፣ ትውልድ አሻጋሪ የሆነው ትምህርት ተጓጉሎ ትውልድ ወደኋላ መቅረቱ ያሳሰባቸው ተቆርቋሪዎች ት/ቤቱን በአዲስ መልክ ለመሥራት፣ የከተማው ነዋሪ ዜጎች፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባለሙያተኞች እናም ሌሎች ተቆርቋሪዎች፣ ከሀገር ውጭ ደግሞ በፋሲለደስ መረዳጃ ማህበር ስር የተደራጁ ዜጎች ተነጋግረው አስፈላጊው ጥናትና መዋቅር ከተዘጋጀ በኋላ፣ በውጭ አገር ግን የት/ቤቱን ሥራ በሚመለከት ከፋሲለደሰ መረዳጃ በላይ ሰፋ በማለት አዲስ አሰተባባሪ ቡድን በማዋቀር እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡
ማሳሰቢያ በጎፈንድሚ የሚለግሱ ከሆነ
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.